አላማችን
በቤተሰብ ፤ በማህበረብ በሀገር ላይ መልካሞ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ ወንድሞችን በማፍራት የወገን አለኝታነትን በተግባር ማረጋገጥ
Our Vison
To create a Strong and Dynamic unity among Brothers who are willing to bring about a Positive Impact on Families, Communities and Nations at Large.
About Addis Tesfa
Addis Tesfa Brothers Unity is a non-profit organization incorporated under the laws of the state of Minnesota. This organization has been created exclusively for purposes subsequent to section 501(c) (3) of the internal revenue code. The name Addis Tesfa, meaning, New Hope, in english, signifies and symbolizes the optimism we have to bring about a significant change in the life of our families, communities and society.
ስለ አዲስ ተስፋ የወንድሞች ህብረት
አዲስ ተስፋ የወንድሞች ህብረት በሚኒሶታ የትርፍ አልባ ድርጅት ማቋቋሚያ ህገ ደንብ መሰረት ህጋዊ ፍቃድ በማግኘት የተቋቋመ ምግባረ ሠናይ ድርጅት ነው። የህብረቱም ዓላማና ተግባር በሀገር ዉስጥ ገቢ መስሪያቤት ደንብ ቁጥር 501(ሲ)(3) በሚፈቅደው መሰረት ለሚከናወን ተግባር ብቻ የሚውል ይሆናል። ይህ ህብረት ከማንኛውም የዕምነት፤ የዘር፤ የቀለምና የፖለትካ ልዩነት ገለልተኛ በመሆን የድርጅቱን ዓላማና ግብ ከሚደገፉ ግለሰቦችም ሆነ ድጋፍ ከሚሰጡ ተቋማት በሚገኝ ገቢ የሚንቀሳቀስ ግብረሰናይ ድርጅት እንጅ ለትርፍ የሚሰራ ተቋም እይደለም ።
ይህ የወንድሞች ህብረት ለተቋቋመበት ዓላማና የስራ ክንዋኔ የሚያገለግል የመተዳደሪያ ደንብና ግልፅ የሆነ የራሱ ራዕይና ተልዕኮ ያለው ማህበራዊ ተቋም ነው። ይህንንም ተቋም ለመምራት ብቃት ያላቸው አምስት አባላት ያሉት የዳይሬክተሮች ቦርድ ያለው ሲሆን ይህም ለማንኛውም የህብረቱ የስራ እንቅስቃሴ ስኬትና ውድቀት ሙሉ ተጠያቂነትና ሃላፊነትን የሚውሰድ አካል ያለው መሆኑን ያረጋግጣል።
አዲስ ተስፋ የወንድሞች ህብረት ስሙ እንደሚገልፀው ወንድሞች በህብረት ሆነው ሲሰሩ በቤተሰብም ሆነ በማህበረሰብ ግልጋሎት ወስጥ ሊያበርክቱት የሚችሉት አስተዋፅዖ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ነው:: ይህንን የወንድሞች ሃይል በተቀናጀና በተደራጀ መልክ በተቋማዊ እመራር ስር በማስተባበር ተገቢውን እውቀትና ስልጠና በመስጠት ከማጀት እስከ አደባባይ ባለው መስክ ሃላፊነታቸውን በሚገባ ሊወጡ የሚችሉ ወንድሞችን ማፍራት ይቻላል። ከዚህም በተጨማሪ በውጭም ሆነ በሃገር ቤት ለሚከናወኑ ማህበራዊና ሃገራዊ ጉዳዮች ከፍተኛ እገዛን ሊያበረክቱ የሚችሉ የላቀ ብቃት ያላቸውን ወንድሞች የማሰባሰቢያ ማዕከል እንደሚሆን ተስፋ አለን፡፡
ያገሩን ሰርዶ ባገሩ በሬ እንደሚባለው የራሳችንን ችግር በራሳችን ለመፍታትና ለወገንም ደራሽ ወገን መሆኑን በመገንዘብ ለተተኪው ትውልድ አሻራ ጥሎ ለማለፍ ፍላጎት ባሳደሩና በቅን መንፈስ በተነሳሱ በሚኒሶታ በሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ወንድሞች አማካይነት የአዲስ ተስፋ ህብረት እንደ አውሮጳውያኑ አቆጣጠር በ 2019 ጥር ወር ተመስርቷል፡፡ በእኛ እምነት የዚህ ህብረት ምስረታ ዕውነተኛ የወገንና የሃገር ፍቅር ስሜት በተግባር የሚለካበትን መልካም ዕድል የሚፈጥርና ብዙ በጎ አድራጊዎችም ለዘመናት ያጡትን ተአማኒነት፣ ግልፀኝነትና ህጋዊ ተጠያቂነት ያለው በአገር ልጆች የሚመራ ተቋም የማግኘት የዘመናት ምኞትን የሚያሳካ መሆኑን እያበሰርን ይህም በብዙ ወገኖች የሚደገፍና የሚጠናከር ስለመሆኑ ገና ከጅምሩ የተገኘው የወንድሞች ምስጋናና ቅቡልነት በቂ ምስክር ነው፡፡
ወገንንም ለመርዳት ሆነ ሃገርንም ለማልማት በተቋማዊ ብቃትና በንቁ ተሳትፎ በህብረት ካልተንቀሳቀስን ውጤታማ ዜጎች እንደማንሆን በመገንዘብ ይህን ህብረት በመቀላቀልና በማገዝ ለወገን ደራሽነታችንንና ለሀገር አለኝነታችንን በተግባር በማስመስከር መጪው ዘመን ስለ ሃገራችን እድገትና ብልፅግና የሰነቀውን ብሩህና አዲስ ተስፋ እውን ለማድረግ በህብረትና በቅንነት እንነሳ።
Board of Directors

Chairman

Chief Financial Officer (CFO)

Secretary

Chief Risk Managment
Officer (CRMO)

Chief Research &
Development Officer (CRDO)